የማረጋገጥ ስትራቴጂ

ማረጋገጥ ከብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎቶች እና በጠያቂው አካል የሚጋራውን መረጃ የእውነተኛ ጊዜ ምላሽ የሚጠይቅ ወሳኝ መስፈርት ነው። ዲጂታል ማረጋገጫ የሚከናወነው በኦንላይን ላይ ወይም ከኦንላይን ውጭ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ነው። ይህንን ለማስተዳደር ቅልጥፍናን እና ተገኝነትን ለማሻሻል የተከፋፈለ አካሄድ ይከተላል እንዲሁም በፕሮግራሙ የተገለጹትን የግላዊነት መርሆዎች ለመጠበቅ የመረጃ መጋራት አካሄድን የሚቆጣጠር መመሪያ ተቀምጧል።

የግል መረጃ ጥበቃ (PDP) ህግ [https://id.gov.et/documents/] በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲፀድቅ በግምገማ ላይ ነው። “ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህግ” እየተዘጋጀ እና በአሁኑ ወቅት በየሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲገመገም እየተደረገ ነው። እነዚህ ረቂቅ አዋጆች የኢፌዲሪ ፓርላማ ሲያፀድቅ (የሚፈለገው አሰራር ሲጠናቀቅ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው) የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ መርሃ ግብር አፈፃፀም የህግ ማዕቀፍ እና በቀጣይም የማረጋገጫ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የፋይዳ መታወቂያ ማረጋገጥ አገልግሎት እንዴት አጋር ድርጅቶችን ይመጥማል? 

አማርኛ