የመረጃዎች ዝርዝር

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ልዩ ማንነትን ለመመስረት የሚያስፈልጉትን መረጃዎችን ብቻ ይሰበስባል። በ NID ዳታቤዝ ውስጥ የተከማቸ እና/ወይም በመታወቂያ ውስጥ የታተመ ሁሉም የተሰበሰበው መረጃ የሚያተኩረው የአንድን ግለሰብ ልዩ ማንነት ለመለየት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ላይ ብቻ ነው።

አስፈላጊ መረጃዎች

ሙሉ ስም

የትውልድ ቀን

ጾታ

አሁን የሚኖሩበት አድራሻ

አማራጭ መረጃዎች

ስልክ ቁጥር

የኢሜይል አድራሻ

የቤት ቁጥር

ሌሎች መረጃዎች

ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት ለማይችሉ፣ የማደጎ ወይም የህጋዊ አሳዳጊያቸው የመታወቂያ ቁጥር በመታወቂያቸው ላይ ይመዘገባል።

ማንኛውንም አይነት የማረጋገጫ ሰነድ እንደማስረጃ ማቅረብ ለማይችሉ ግለሰቦች በስርአቱ ውስጥ ከተመዘገበ ሰው ምስክርነት ማግኘት የችላሉ።

የዜግነት ሁኔታ በከፊል ግዴታ ሲሆን፣ የዜግነት ማረጋገጫ ያላቸው እንደ ኢትዮጵያውያን ወይም የውጭ ዜጎች በዜግነታችው እንዲመዘገቡ እንዲሁም ምንም ማረጋገጫ የሌላቸው ደግሞ ደረጃቸው “ያልታወቀ” ተብሎ የመዘገባሉ።

የባዮሜትሪክ ውሂብ 10 የጣት አሻራዎች (4-4-2 ቅኝት)፣ የሁለት አይኖች አይን አሻራ ስካን እንዲሁም ከ ICAO ጋር ተኳሃኝ የሆነ ፎቶ መሰብሰብ ግዴታ ነው።  ማየት ለተሳናቸው ሰዎች፣ እጅ ወይም ጣት ለጎደላቸው ወእም በተፈጥሮ ምክንያት በእነዚያ የአካል ክፍሎች ላይ በደረሰ አካላዊ ጉዳት የባዮሜትሪክ ውሂብ ሊነበብ በማይችልበት ጊዜ የልዩነት ማረጋገጫው ለወደፊቱ በማስረጃነት ፎቶግራፍ ተነስቶ ይያያዛል።

አማርኛ