በተደጋጋሚ የሚጠየቁ
Frequently Asked Questions
Questions
2. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ የሆነው ማነው?
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በ “ረቂቅ አዋጁ” ነዋሪ የሚገለፀው “በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።” ይህም የሚያካትተው ፡-
- ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ.
ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል። - ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
- የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ።
- የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች ፣ የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
- ማንኛውም ለምዝገባ ብቁ የሆነ ሰው id.et/proof ላይ በተጠቀሰው መሰረት ተቀባይነት ያለው የማንነት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል።