የፋይዳ ቁጥር 

የምዝገባ ሂደት በተሳካ ሁኔታ ከተካሔደ በኃላ ነዋሪዎች ለተጨማሪ መለያዎች የሚያገለግል ልዩ ቁጥር ይሰጣቸዋል ። ፋይዳሲስ (Faydasis) – ልዩ ቁጥሩ ለአንድ ግለሰብ እንደሚሰጥ እና በየትኛውም ጊዜ ከሱ ውጪ ሌላ ለማንም እንደማይሰጥ የምዝገባ ስርአቱ ዋስትና ይሰጣል።

 

ፋይዳ መለያ ቁጥር (FIN)

ይህ ቁጥር ቋሚ እና በዘፈቀደ (randomly) የተመሰረተ ባለ 12-አሃዝ ቁጥር ነው። የምዝገባ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እንደተጠናቀቀ ለእያንዳንዱ ነዋሪ በልዩ ሁኔታ ይሰጣል። ይህም ቁጥር ለህይወት ዘመን የሚያገለግል ሲሆን ለግለሰቡ አንዴ ከተሰጠ በኃላ ቁጥሩ አይቀየርም

 

ነዋሪዎቹ የዲጂታል መታወቂያን አገልግሎት ሲጠየቁ ብቻ እንዲጠቀሙ እና ለሌላ ሰው ባያጋሩ ይመከራል።

 

የፋይዳ ካርድ ቁጥር - FCN

ከአንድ የፋይዳ መለያ ቁጥር (FIN) ጋር በተገናኘ መታወቂያ ካርድ ላይ የሚታተም ባለ 16-አሃዝ የዘፈቀደ ቁጥር ሲሆን አዲስ ካርድ እንደገና በሚታተም ቁጥር ይህ ቁጥር ይቀየራል።

ነዋሪዎች ይህን ቁጥር ከታማኝ አጋር ጋር ለኦንላይን ማረጋገጫነት እንዲጠቀሙ ይመከራሉ።

ፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር - FAN

ይህ ከፋይዳ መለያ ቁጥር ጋር የተያያዘ ባለ 16 አሃዝ ቁጥር ነው።  የፋይዳ ልዪ ቁጥር (FIN) ጥያቄ መሰረት ባለቤትነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ቁጥሩ ሊፈጠር ይችላል። እንዲሁም ባለቤቱ ለተወሰነ ጊዜ ከተገለገለበት በኃላ በማንኛውም ጊዜ በፈቃዱ ሊሻር ይችላል።

የአሊያስ ቁጥሩ ግለሰቦች ከየትኛውም አጋሮች ጋር ራሳቸውን ለማረጋገጥ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ነዋሪዎች ማንነታቸውን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ይህንን ቁጥር እንዲጠቀሙ ይመከራሉ።

 

አማርኛ