ፋይዳ ለሁሉም የኢትዮጵያ ነዋሪዎች!

 

የፋይዳ ምዝገባ ሒደት ቀላል እና ፈጣን ነው። አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ በአማካኝ በ 10 ደቂቃ ምዝገባውን ያጠናቅቃሉ አሊያም በኦንላይን ቅደመ-ምዝገባ በማድረግ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

ለፋይዳ መመዝገብ ከክፍያ ነጻ ሲሆን በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ። በአከባቢዎ አቅራቢያ የሚገኝ የምዝገባ ማእከል ሊኖር የሚችልበት ዕድል ከፍተኛ ነው እባክዎን ምቹ የመመዝገቢያ ማእከልዎን ለማግኘት ይፈልጉ።

ኦንላይን ቀጠሮ ይያዙ

ኦንላይን ቅደመ-ምዝገባ በማድረጎት ወረፋ መጠበቅን ይቀንሳሉ። ኦንላይን ተጠቅሞ በመመዝገብ ጊዜዎን ይቆጥቡ።

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለማግኘት ምን ያስፈልጋል?

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለማግኘት ዲሞግራፊክ እና ባዮሜትሪክ መረጃዎን መስጠት ይኖርቦታል። 

Fayda Enrollment Process

የፋይዳ የምዝገባ ሒደት

የፋይዳ የምዝገባ ሒደት ዴሞግራፊክ መረጃን በመስጠት ይጀምራል (ሙሉ ስም፣ ጾታ፣ የትውልድ ቀን፣ አሁን ያሉበት አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ) እና የባዮሜትሪክ መረጃ (10 የጣት አሻራ፣ 2 የአይን ብሌን አሻራ እና የፊት ፎቶ)።

ተመዝጋቢዎች ምዝገባውን በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኃላ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር በስልክ ቁጥራቸው ወይንም በኢሜል አድራሻቸው ይላክላቸዋል።

አማርኛ